Skip to content

Ethiopia Hagere

Sections
Personal tools
You are here: Home » * Austria Vienna * » Rally in Vienna » Second Rally in Vienna

Second Rally in Vienna

Document Actions

ቪዬና ያሉ ኢትዮጵያውያን ንዴታቸውንና ሀዘናችውን ለማሰማት ረቡእ ከሰአት በኋላ ከሰምንት ሰአት እስከ 11 ሰአት ዳግም አደባይባይ በመውጣት ቁጣችውንና ንዴታችወን ለአውሰትሪያ ሕዝብ አሰምተዋል፡፡

በፓረላማ አማካይ በሆነው ቦታ ደጋፍ ማሕብሮችና ታዋቂ ግለስቦችን በምክትል ፓርላማ ፕረዘዳንቷ በጋበዙበት ቦታ አንዲሁም በፕረዘዳንቱ ቢሮ    በጠቅላይ ሚንስተሩ ቦታ አና በ ውጭ ጉዳይ ሚንስተሩ በኩል በማለፍ አገራችን  አሁን ያለችበትን ቀውሰ ሁኔታ በማሰረዳት፣ የመለሰ መንግሰት ለዚህ

ተጠያቂ መሆኑን በመግለጽ ሰልጣን ቶሎ እነዲለቅና ሰላምና መረጋጋት በኢትዮጵያ እንዲስፍን ምኞታችውን ለተመልካች በይፋ አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻ ወደ አውሰትሪያ እረዳታ ሰጭ ድርጅት መሰሪያ ቤት በመጓዋዝ እረዳታ ለጊዜውለመለስ መንግስት ካውሰትሪያና ካወሮፓ መለስ  እሰከገዛ ድረሰ እንዲቆም ጠይቀዋል.፡፡

በታሪካችን ዛሬም ቢሆን እንደ ድሮው ነጻነታችን ካለማንም እረዳታ ጠብቀን እንደቆየን ሁሉ የድሞክራሲ መብታችንንም አንደምንጠብቅ ባለሙሉ ተሰፋ ነን በማለት መፈክራችወን አሰምተው የአሜሪካና የአውሮፓ መንግሰታት በተቃዋሚ ፓረቲ ላይ የሚያድረጉትን   ጫና አጥብቅው አውግዘዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ልክ እንደ ዩክሬን መሆኑን በማሰመለከት ያውሮፓንና ያሜሪካን መንግሰት፣  የመለሰን መንግስት ስልጣን እንዲያስረክብ እንዲያሰገድዱ፣ የመለሰን መንግሰት እሹሩሩ ከማለት እንዲቆጠቡና ዲሞክራሲ ስራት እንዲከተሉ ተቃራኒ ፓረቲውን ልክ እነደ ዩክሬን እንዲደግፉ አቤቱታ አቅረበዋል፡፡

መለሰ ለመሸነፉ የአዲሰ አበባ ውጤት ብቻ በቂ ነበረ በማለት *በአንደ አፍ ሁለት ምላስ* የተባልውን ያበው ምሳሌ በመጥቀሰ እሮሮአችውን አሰምትዋለ፡፡

በመጨረሻም ህይወታቸውን ላጡት ታላቅ ኢትዮጵያዊያን የሂሊና ጸሎት አድረግው የታስሩት ጀግኖች በቅጽበት እንዲፈቱ ጠይቅው ተቃዋሚ ፓረቲው ሰልጣን ለመያዝ ተዘጋጅቶ በተጠንቀቅ እንዲቆም አሳሰብዋል፡፡

በተለይም ጀግኖችን የኢትዮጵያ አየር ሀይል አብራሪዎችን በጅቡቲና በላሩሰ የሚገኙትን፣  የዩኒቭረሲቲ ተማሪዎችንና  ታኪሰ ነጂዎች ባድርጉትና በሚያድረጉት ትግልና  ተጋድሎን በማድነቅ ለቀረው ሰራዊትና  ህዝብ  ምሳሌ ይሆናሉ በማለት ታላቅ ጭብጨባና አክበሮት በመሰጠት አወድስዋል፡፡

እንዲሁም ተቅዋሚ ፓረቲዎች ያደርጉትን ስራ፣ ያገኙትን ውጤት ያሳዩት ሀላፍነትን በማድነቅ ሀገራችንን ሊመሩ ብቃት ችሎታና  የሕዝብ ፍቅር አላችው በማለት የአለም ሕዝብ እንዲቀብላችወ ተማጽነዋል፡፡

 

 

 

 

goto Photo Gallery

 

 

Created by am69208
Last modified 2005-07-01 16:21
 

Powered by Plone

This site conforms to the following standards: