Skip to content

Ethiopia Hagere

Sections
Personal tools
You are here: Home » * Austria Vienna * » Fundraising Event

Fundraising

Document Actions


                                                             ምስጋና

     በወቅቱ የነበረው ዝናብና የቦታው እርቀት ሳያግዳቸው ወገኔ በጠራኝ እሮሮ ላይ እኔም ተገኝቼ የተቻለኝን አስተዋጾ ማድረግ አለብኝ ብላችሁ ከከተማም ሆነ ከገጠር ለመጣችሁ ብርቅዬ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሃገር ዜጎች ሁሉ በአዘጋጁ ስም ሆኜ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ::

እንደምናውቀው በአገራችን ልጅ ተስፋ ነው:: እረዳትም ነው:: ጧሪም ነው:: ሆኖም ግን በፋሽሽቱ መለስ አዛዥነት በአጋዚ ጦር እረሻኝነት አብዛኛው የአገሪቱ እናቶችና አባቶች ልጆቻቸውን አጥተው ከመቼውም ይበልጥ እያለቀሱ ይገኛሉ:: ወግኔ ዝም አትበል ፣ ኢርዳኝ ፣ ድረስልኝ፣ ከዚህ የችግር ጨለማ አውጣኝ እያሉ ነው::

       ይህ የወገን እሮሮና የድረሱልኝ ጥሪ አክብራችሁና በቦታው ተገኝታችሁ ባደረጋችሁት ትልቅ ተሳትፎ ከወጭ ቀሪ 1725,00  ኦይሮ ተገኝቶአል :: ምንም እንኳን የገንዘቡ መጠኑ የሁሉንም እናቶች እንባ ማድረቅ ባይቻልም አንድ ቀንም ኑሮ በመሆኑ ለተወሰኑትና በጣም በአሁኑ ሰዓት ችግር ላለባቸው ቤተሰቦች ኢሰመጉን በማማከር በቀጥታ ለቤተሰቦቹ የሚደርስበትን ሁኔታ ኮሚቴው በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ በቪየና ለሚገኙ አገር ወዳዱ ኢትዮጵያውያን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው::

      ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ገና ለመርዳት ቃል የገቡልንን ሰዎች አይጨምርም:: ገንዘቡ እንደደረሰን እናሳውቃችኋለን:: በተጨማሪ በወቅቱ በተለያየ ምክንያት ያልነበራችሁ ለመርዳት የምትፈልጉ ካላችሁ ኮሚቴውን በስልክ ወይም በኢሜል ልታሳውቁ ትችላላችሁ::

 

Bank für Arbeit und Wirtschaft

BAWAG , Konto Nr 03410903511,  BLZ 14000

 

 

Created by am69208
Last modified 2005-07-29 00:38
 

Powered by Plone

This site conforms to the following standards: